Daily Weather Report 25 Jan 21
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ በመሆኑም በዳንግላ 4.5፣ በወገልጤና 1.8፣ በባቲ 3.0፣ በመሀልሜዳ 0.5፣ በደብረብርሀን 0.0፣ በሾላገበያ 3.1፣ በእምድብር 4.6፣ በቢሾፍቱ 4.0፣ በቡኢ 3.6፣ በአርሲ ሮቤ 2.5፣ በባሌ ሮቤ 4.0፣ በሐሮማያ -0.4 እና በጅግጅጋ 0.2 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን በቴፒ እና በአማን ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል::
Yesterday, the Bega dry, sunny and windy weather conditions was observed in the northwest, northeast, central, southern highlands and eastern areas of our country. Thus, the minimum temperature of the day was recorded below 5oC in Dangla 4.5, Wegeltena 1.8, Bati 3.0, Mehalmeda 0.5, Debre Birhan 0.0, Shola Gebeya 3.1, Emdibir 4.6, Bishoftu 4.0, Bui 3.6, Arsi Robe 2.5, Bale Robe 4.0, Haramaya -0.4 and Jigjig 0.2 the minimum temperature of the day was recorded below 5oC. On the other hand, there was cloud cover over the southwestern parts of the country; accordingly light amount rain was recorded in Tepi and Aman.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ይስተዋላል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በደባርቅ፣ በዳንግላ፣ በወገልጤና፣ በመሀል ሜዳ፣ በአምባማሪያም፣ በሾላገበያ፣ በአለምከተማ፣ በደብረብርሀን፣ በቡኢ፣ በአርሲሮቤ፣ በባሌሮቤ፣ በሐሮማያ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡
For the next day, the Bega dry, sunny and windy weather conditions will be observed over most parts of our country. In association with this, the minimum temperature of the day will be below 5°C in Debark, Dangla, WegelTena, Mehalmeda, Ambamariam, Shola Gebeya, Alemketema, Debre Beirhan, Bui, Arsi Robe, Bale Robe, Haramaya and Jigjiga. On the other hand, there will be occasional cloud cover over the southwest and southern parts of the country.