Daily Weather Report 25 Jan 20

Weather Summary for previous day

Jan. 19, 2025

በትናንትናው ዕለት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ አመዝኖባቸው ውሏል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በዳንግላ 4.0፣ በወገልጤና 1.4፣ በባቲ 3.1፣ በመሀልመዳ 1.2፣ በአለምከተማ 4.5፣ በእነዋሪ 4.5፣ በደብረብርሀን 0.2፣ በሾላገበያ 4.0፣ በቡኢ 2.4፣ በአርሲሮቤ 3.5፣ በባሌሮቤ 4.8፣ በጅግጅጋ 0.2 እና በሐሮማያ 1.8 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the dry, sunny, and windy weather of the Bega was observed in most parts of the country. In this regard, the daily minimum temperature dropped below 5°C in Dangila 4.0, Wegeltena 1.4, Bati 3.1, Mehalmeda 1.2, Alemketama 4.5, Enewari 4.5, Debrebrehan 0.2, Sholagebeya 4.0, Bui 2.4, Arsirobe 3.5, Balerobe 4.8, Jigjiga 0.2 and Haromaya 1.8.

Weather Forecast for next day

Jan. 21, 2025

በነገው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ ስለሆነም በዳንግላ፣ በማይጨው፣ በወገልጤና፣ በባቲ፣ በመሀልሜዳ፣ በደብረብርሀን፣ በአለምከተማ፣ በሾላገበያ፣ በቢሾፍቱ፣ በቡኢ፣ በእምድብር፣ በአርሲሮቤ፣ በባሌሮቤ፣ በሐሮማያ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ይሁን እንጂ በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, the Bega dry, sunny, and windy weather will be observed in the northeast, central, southern highlands, and eastern parts of our country. As a result, the numerical weather forecast information indicates that the day’s minimum temperature may drop below 5°C in Dangila, Maichew, Wegeltena, Bati, Mehalmeda, Debrebrehan, Alemketema, Sholagebeya, Bishoftu, Bui, Emdibir, Arsirobe, Balerobe, Haromaya and Jigjiga. However, there will be cloud coverage in the southwestern parts of the country.