Daily Weather Report 25 Jan 17
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በማይጨው 3.2፣ በወገልጤና 1.8፣ በደብረወርቅ 5.0፣ በአምባማሪያም 5.0፣ በአለምከተማ 4.0፣ በመሀልሜዳ 3.2፣ በደብረብርሀን 2.2፣ በሾላገበያ 2.0፣ በቢሾፍቱ 4.4፣ በቡኢ 3.0፣ በጅማ 5.0፣ በአርሲሮቤ 4.0፣ በባሌሮቤ 3.8፣ በሐሮማያ 3.8 እና በጅግጅጋ 3.2 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the dry, sunny, and windy weather of the Bega was observed in most parts of the country. Accordingly, the daily minimum temperature dropped below 5°C in Maichew 3.2, Wegeltena 1.8, Debrework 5.0, Ambamariam 5.0, Alemketema 4.0, Mehalmeda 3.2, Debrebrehan 2.2, Sholagebeya 2.0, Bishoftu 4.4, Bui 3.0, Jimma 5.0, Arsirobe 4.0, Balerobe 3.8, Haromaya 3.8 and Jigjiga 3.2.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በአብዛኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በማይጨው፣ በደባርቅ፣ በወገልጤና፣ በአምባማሪያም፣ በመሀልሜዳ፣ በባቲ፣ በደብረብርሀን፣ በእንዋሪ፣ በአለምከተማ፣ በሾላገበያ፣ በቢሾፍቱ፣ በቡኢ፣ በእምድብር፣ በአርሲሮቤ፣ በባሌሮቤ፣ በሐሮማያ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡
For the upcoming day, the Bega dry, sunny, and windy weather will prevail in most parts of our country. Thus, the forecast information indicates that the day’s minimum temperature may drop below 5°C in Maichew, Debark, Wegeltena, Ambamariam, Mehalmeda, Bati, Debrebrehan, Enewari, Alemketema, Sholagebeya, Bishoftu, Bui, Emdibir, Arsirobe, Balerobe, Haromaya and Jigjiga. On the other hand, there will be occasional cloud coverage in the country's southwestern areas.