Daily Weather Report 25 Jan 13
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በደባርቅ 4.5፣ በዳንግላ 4.5፣ በአምባማሪያም 4.0፣ በሾላገበያ 3.0፣ በቡኢ 5.0 እና በጅግጅጋ 4.8 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጥቂት የደቡብ ምዕራብ እና ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆንና በኮምቦልቻ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል::
Yesterday, the Bega dry, sunny, and windy weather was observed over the northwestern, central, and eastern parts of the country. In line with this, the daily minimum temperature dropped below 5°C in Debark 4.5, Dangila 4.5, Ambamariam 4.0, Sholagebeya 3.0, Bui 5.0 and Jigjiga 4.8. Conversely, cloud coverage was observed in a few parts of the southwest and northeast of the country, accordingly light rain was recorded in Kombolcha.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ይስተዋላል፡፡ ስለሆነም በደባርቅ፣ በዳንግላ፣ በአዴት፣ በአምባማሪያም፣ በሾላገበያ፣ በአለምከተማ፣ በአርሲሮቤ እና በባሌሮቤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ ይሁን እንጂ በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሸካ እና ከፋ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
For the upcoming day, the Bega dry, sunny, and windy weather will prevail in most parts of our country. Consequently, the forecast information indicates that the day’s minimum temperature may drop below 5°C in Debark, Dangila, Adet, Ambamariam, Sholagebeya, Alemketema, Arsirobe and Balerobe. However, there will be cloud coverage over the southwestern and northeastern parts of the country, with light rainfall expected in a few places of the Sheka and Kefa zones.