Daily Weather Report 25 Jan 11
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በጅማ፣ ጎሬ፣ ሰኮሩ፣ ተርጫ፣ አማን፣ ሳውላ፣ አርባ ምንጭ እና ዲላ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመካከለኛዉ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዉሎባቸዋል ሲሆን በሾላ ገበያ 3.0፣ በዳንግላ 5.0 እና በደባርቅ 4.5 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ50c በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over the south and southwest parts of the country. In association with this, light amounts of rainfall were recorded in Jimma, Gore, Sekoru, Tercha, Amman, Sawla, Arba Minch and Dilla. On the other hand, the Belg dry, sunny and windy weather was observed in the central and northwestern parts of the country, with the minimum temperature of the day recorded below 5oC Shola Gebeya, Dangla 5.0 and Debark 4.5.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምስራቅ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ እና ፋንቲ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳውሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስከቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ አማሮ እና ጌዲኦ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ በሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ በመሆኑም በደባርቅ፣ በዳንግላ፣ እና ሾላ ገበያ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the southwest, south, northeast and central areas of our country. In association with this, the from Tigray region eastern, southeastern, and east zones; from Amhara region north and south Wollo zones; zones from Afar region Kilbetti and Fanti; from Oromia region Jimma, west Arsi, Guji, and West Guji; from southwest Ethiopia region Kefa, Bench Sheko, west Omo, Dauro and Konta zones; Sidama Regional zones and from Southern Ethiopia region of Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, south Omo, Amaro and Gedeo zones will receive light to moderate amounts (1-29 mm) of precipitation. However, the Belg dry, sunny and windy weather condition will be observed over the northern, northwest and eastern parts of the country. Accordingly, the minimum temperature for the day will be below 5oC in Debark, Dangla, and Shola Gebeya.