Daily Weather Report 25 Jan 10
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ንፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዳንግላ 4.5፣ በአምባ ማርያም 4.0፣ በጅግጅጋ 4.2 እና በሾላ ገበያ 4.5 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጥቂት የደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆንና በማሻ፣ ጅማ፣ ቦሬ እና ሞያሌ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል::
Yesterday, the Bega dry, sunny and windy weather condition was observed in the northeast, east and northwestern parts of our country. In association with this, the minimum temperature of the day was recorded below 5oC in Dangla 4.5, Amba Maryam 4.0, Jigjiga 4.2 and Shola Gebeya 4.5.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በደቡብ ምዕራብ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና በሰሜን ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ ምዕራብ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ እና ቦረና ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ፣ ቤንች ሸኮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ዳውሮ እና ኮንታ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀድያ፣ ስልጤ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታና ጠንባሮ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ባስከቶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች እና ከአማራ ክልል ሰሜን እና ደቡብ ወሎ፣ ደቡብ ጎንደር እና ምስራቅ ጎጃም ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ በመሆኑም በደባርቅ፣ በዳንግላ እና ሾላ ገበያ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow there will be cloud cover over the southwest, southern, central and northeastern parts of our country. In association this, from Oromia region Jimma, west Arsi, Guji, west Guji, Bale and Borena zones; from the Central Ethiopia Region Kefa, Bench Sheko, west Omo, Dauro and Konta zones; from central Ethiopia region Hadia, Silte, Yem Special Zone, Kembata and Tembaro zones; Sidama regional zones and from Southern Ethiopia region Wolaita, Gofa, Basketo, South Omo and Gedeo zones, and from Amhara region north and south Wollo, south Gondar and east Gojjam will receive light amounts of rain. On the other hand, the Bega dry, sunny and windy weather condition will be observed over the northern, northwest and eastern parts of the country. In this regards, forecast information suggest that the minimum temperature of the day will be below 5oC in Debark, Dangla and Shola Gebeya.