Daily Weather Report 25 Jan 09

Weather Summary for previous day

Jan. 8, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣በመካከለኛዉ፣ በሰሜን ምዕራብ እና በደቡብ ከፍተኛ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ፀሀያማ እና ንፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዳንግላ 4.5፣ በሾላ ገበያ 4.5 እና በጅግጅጋ 4.2 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ50c በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በደቡብ እና ደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን በማሻ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday the northeast, east, central, northwest and southern highlands of the country experienced dry, sunny and windy weather. In addition, the lowest daily temperature was recorded below 50c in Dangila 4.5, Shola Gebeya 4.5 and Jigjiga 4.2. On the other hand, the south and southwest parts of the country had cloud coverage and light rain was recorded in Masha.

Weather Forecast for next day

Jan. 10, 2025

በነገዉ ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች፣ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ፣ አርሲ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ እና ቦረና ዞኖች፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል የጉራጌ፣ ሀድያ፣ ስልጤ፣ ከምባታና ጠንባሮ ዞኖች፣ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስከቶ፣ ደራሼ፣ አማሮ እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ የሰሜን ሰሜን ምዕራብ፣ምዕራብ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ደረቅ፣ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም በአድግራት፣ በማይጨዉ፣ በዳንግላ፣ ሾላ ገበያ፣ በሐሮማያ፣ በአርሲ ሮቤ፣ በቢሾፍቱ፣ በባሌ ሮቤ እና በቡኢ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ50c በታች እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

For tomorrow, there will be cloud coverage over the southern, southwestern and north-eastern parts of the country. In addition, light rain will be expected over the northern and southern Wollo zones of Amhara region, the Jimma, Arsi, Guji and West Guji, Bale and Borena zones of Oromia region, the Gurage, Hadiya, Silte, Kambata and Tambaro zones of Central Ethiopia region, and the Gamo, Gofa, Basketo, Derashe, Amaro of Southern Ethiopia region and all Sidama zones. However, dry, sunny and windy weather will prevail over the northern, northwestern, western and eastern parts of the country. Therefore, numerical forecast data indicates that the daily minimum temperature in Adigrat, Mai chewu, Dangila, Shola gebeya, Haromaya, Arsi Robe, Bishoftu, Bale Robe, and Bui will be below 50c.