Daily Weather Report 25 Jan 08

Weather Summary for previous day

Jan. 7, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁም ጋር ተያይዞ በባቲ 3.6፣ በዳንግላ 4.7፣ በመሐል ሜዳ 2.2፣ በደብረብርሀን 3.8፣ በቢሾፍቱ 3.2፣ በቡኢ 4.0፣ በአርሲ ሮቤ 3.0 እና ቦሬ 5.0 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the dry, sunny and windy Bega weather was observed in the north-eastern, central and southern high areas of our country. Along with this, in Bati 3.6, Dangla 4.7, Mehal Meda 2.2, Debre Berhan 3.8, Bishoftu 3.2, Bui 4.0, Arsi Robe 3.0 and Bore 5.0, the minimum temperature of the day was recorded as below 5oC.

Weather Forecast for next day

Jan. 9, 2025

በነገዉ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማው የአየር ሁኔታ እንደሚስተዋልባቸው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሾላ ገበያ፣ በእንዋሪ፣ በደባርቅ፤ በወረኢሉ፣ በወገል ጤና፣ በሐሮማያ፣ በአርሲ ሮቤ፣ በቢሾፍቱ፣ በባሌ ሮቤ እና በቡኢ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ይሁን እንጂ በመካከለኛው፣ በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆንና በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow Forecast data indicates that the dry, sunny and windy weather of the Bega will be observed in the northeastern and eastern areas of our country. In connection with this, Shola Gebeya, Enewari, Debark; Numerical forecast data indicates that the minimum temperature of the day will be below 5oC in Wareilu, Wegel Tena, Haromaya, Arsi Robe, Bishoftu, Bale Robe and Bui. However, there will be cloud cover in the central, western and southwestern areas of our country and there will be a small amount of rain in some places.