Daily Weather Report 25 Jan 06

Weather Summary for previous day

Jan. 5, 2025

በትናንትናው ዕለት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ አመዝኖባቸው ውሏል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ በደባርቅ 4.5፣ በዳንግላ 4.8፣ በወገልጤና 2.0፣ በባቲ 4.6፣ በአምባማሪያም 4.6፣ በመሀልመዳ 4.2፣ በአለምከተማ 4.0፣ በእነዋሪ 4.5፣ በደብረብርሀን 1.2፣ በሾላገበያ 3.0፣ በቢሾፍቱ 4.0፣ በቡኢ 3.0፣ በአርሲሮቤ 3.0፣ በባሌሮቤ 4.8 እና በሐሮማያ 2.2 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአማን ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the Bega dry, sunny, and windy weather was observed across most parts of the country. In this regard, the daily minimum temperature dropped below 5°C in 5°C in Debark 4.5, Dangila 4.8, Wegeltena 2.0, Bati 4.6, Ambamariam 4.6, Mehalmeda 4.2, Alemketema 4.0, Enewari 4.5, Debrebrehan 1.2, Sholagebeya 3.0, Bishoftu 4.0, Bui 3.0, Arsirobe 3.0, Balerobe 4.8 and Haromaya 2.2. Conversely, cloud coverage was observed over the southwestern parts of our country; in line with this light rain was recorded in Aman.

Weather Forecast for next day

Jan. 7, 2025

በነገው ዕለት የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ይስተዋላል፡፡ ስለሆነም በአይደር፣ በአፅቢ፣ በማይጨው፣ በደባርቅ፣ በዳንግላ፣ በወገልጤና፣ በአምባማሪያም፣ በመሀልሜዳ፣ በኮምቦልቻ፣ በደብረብርሀን፣ በእንዋሪ፣ በአለምከተማ፣ በሾላገበያ፣ በፍቼ፣ በቢሾፍቱ፣ በቡኢ፣ በአርሲሮቤ፣ በባሌሮቤ፣ በሐሮማያ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች የሚስተዋልባቸው ሲሆን የማለዳና የሌሊት ቅዝቃዜ በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚቀጥል የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡

For the upcoming day, the Bega dry, sunny, and windy weather will prevail in most parts of our country. Thus, the forecast information indicates that the day’s minimum temperature may drop below 5°C in Aider, Atsebi, Maichew, Debark, Dangila, Wegeltena, Ambamariam, Mehalmeda, Kombolcha, Debrebrehan, Enewari, Alemketama, Sholagebeya, Fiche, Bishoftu, Bui, Arsirobe, Balerobe, Haromaya and Jigjiga, with cold conditions persisting in the same manner in the morning and night cold will continue in the same conditions. On the other hand, there will be cloud coverage over the southwestern parts of the country.