Daily Weather Report 25 Jan 02
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ እና በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዉሎባቸዉ ሲሆን በማይጨው 4.0፣ በደባርቅ 4.2፣ በወገልጤና -1.0፣ በደብረወርቅ 4.4፣ በአለምከተማ 3.8፣ በእንዋሪ 3.1፣ በደብረብርሀን -2.0፣ በቢሾፍቱ 3.0፣ በቡኢ 3.0 እና በጅማ 2.4፣ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, the dry, sunny and windy Bega weather was observed in the north, northeast, central, southern high places and eastern areas of our country. Thus, in Maichew 4.0, Debark 4.2, Wegeltena -1.0, Debrework 4.4, Alem ketema 3.8, Enewari 3.1, Debre Berhan -2.0, Bishoftu 3.0, Bui 3.0 and Jimma 2.4, the lowest temperature of the day was recorded below 5oC the minimum temperature of the day was recorded below 5oC. On the other hand, there was cloud cover over the southwestern parts of our country.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በአብዛኛዉ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ በመሆኑም በደብረ ብርሀን፣ በሾላ ገበያ፣ በእንዋሪ፣ በመሀልሜዳ፣ በወረ ኢሉ፣ በአምባ ማርያም፣ በወገል ጤና፣ ፣ በሐሮማያ፣ በአርሲ ሮቤ፣ በአደሌ፣ በቢሾፍቱ፣ በባሌ ሮቤ፣ በቡኢ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ50C በታች እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅና ደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow Dry, sunny and windy Bega weather will be observed in most parts of our country. Therefore, in Debre Berhan, Shola Gebeya, Enewari, Malmeda, Were Ilu, Amba Maryam, Wegel Tena, Haromaya, Arsi Robe, Adele, Bishoftu, Bale Robe, Bui and Jigjiga Numerical forecast data suggest that the minimum temperature of the day will be below 50C. On the other hand, there will be cloud cover in the northeast and southwest areas of our country.