Daily Weather Report 25 Jan 01
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛዉ፣ በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ በመሆኑም በአዲግራት 3.5፣ በማይጨው 3.5፣ በዳንግላ 4.0፣ በሞጣ 5.0፣ በባህርዳር 2.5፣ በጉንዶ መስቀል 4.4፣ በወገልጤና -0.4፣ በደብረወርቅ 4.2፣ በአለምከተማ 3.2፣ በእንዋሪ 4.2፣ በደብረብርሀን -2.8፣ በፍቼ 3.0፣ በቢሾፍቱ 2.0፣ በቡኢ 2.4፣ በጅማ 1.4፣ በአርሲ ሮቤ 3.0፣ በሐሮማያ 4.2 እና በጅግጅጋ 5.0 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ Yesterday, the dry, sunny and windy Bega weather was observed in the north, northwest, northeast, central, southern high places and eastern areas of our country. Thus, in Adigrat 3.5, in Maichew 3.5, in Dangla 4.0, in Mota 5.0, in Bahir Dar 2.5, in Gundo Meskel 4.4, in Wegeltena -0.4, in Debrework 4.2, in Alem ketema 3.2, in Enewari 4.2, in Debre Berhan -2.8, in Fiche 3.0, in Bishoftu 2.0, In Bui 2.4, Jimma 1.4, Arsi Robe 3.0, Haromaya 4.2 and Jigjiga 5.0, the minimum temperature of the day was recorded below 5oC. On the other hand, there was cloud cover over the southwestern parts of our country.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በአዲግራት፣ በደባርቅ፣ በወገልጤና፣ በባቲ፣ በአምባማሪያም፣ በመሀልሜዳ፣ በደብረብርሀን፣ በእንዋሪ፣ በአለምከተማ፣ በሾላገበያ፣ በፍቼ፣ በቢሾፍቱ፣ በቡኢ፣ በአርሲ ሮቤ፣ በባሌ ሮቤ፣ በሐሮማያ እና በጅግጅጋ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆንና የሌሊት እና የማለደው ቅዝቃዜም ቀጣይነት እንደሚኖረው አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል ሰሜን ሸዋ የአማራ ክልል ዞኖች፣ የአፋር ክልል ዞኖች እና የሶማሌ ክልል ዞኖች የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow Dry, sunny and windy Bega weather will be observed in the north, northwest, west and south parts of our country. Along with this, in Adigrat, Debark, Wegeltena, Bati, Amba Mariyam, Malmeda, Debre Berhan , Enewari, Alem ketema , Shola Gebeya, Forecast data indicates that the minimum temperature of the day will be below 5°C in Fiche, Bishoftu, Bui, Arsi Robe, Bale Robe, Haromaya and Jigjiga, and the night and morning will continue to be cold. On the other hand, North Shewa Amhara region zones, Afar region zones and Somali region zones will have occasional cloud cover in the parts of the country.