Daily Weather Report 25 Feb 28
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አጋማሽ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ እና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአይራ፣ በአርጆ፣ በበደሌ፣ በጋቲራ፣ በጭራ፣ በማሻ እና በወላይታ ሶዶ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ በፉኝዶ፣ በገዋኔ እና በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, enhanced cloud coverage was observed over the country's western half, central, southern, and north eastern parts. As a result, in Aira, Arjo, Bedele, Gatira, Chira, Masha, and Walaita Sodo light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded. In contrast, the day's maximum temperature exceeded 38°C in Metema, Fugnido, Gewane, and Gode.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በአንዳንድ የምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ደቡብ፣ ሰሜን ምዕራብ እና ሰሜን ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ እና ኢሉባቦር ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ እና ከፋ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሁመራ፣ መተማ፣ ዱብቲ፣ ሰመራ፣ መተከል፣ ፓዌ፣ አቦቦ፣ ላሬ፣ ጎዴ እና ቀብሪዳሃር ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38°C በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
For the next day, some areas in the west, south western, south, north western and north eastern of portions of our country are expected to have cloud coverage. Consequently, the Tigray region the southeast and east zones; from Amhara region south Gondar, west and east Gojjam zones; from Oromia region Jimma and Ilubabor zones; from the south west Ethiopia region Sheka and Kefa zones and zones of Sidama region will have light rain in a few places. Conversely, numerical weather forecast information shows that the maximum temperature of the day will exceed 38°C in Humera, Metema, Dubti, Semera, Metekel, Pawe, Abobo, Lare, Gode, and Kebridehar.