Daily Weather Report 25 Feb 26
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ መተማ፣ ገዋኔ እና በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, they had cloud cover in the north-west, central, west and south-west parts of the country. On the other hand, in Gambella, Metema, Gewane and Gode, the maximum temperature of the day was recorded above 38°C.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ከአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ቄለም፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ጅማ፣ ጉጂ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ እና ሸካ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ አቦቦ፣ ፉኝዶ፤ አሶሳ፣ ከማሽ፣ ቡለን፤ በመተማ፣ ቋራ፤ ጎዴ፣ ቀብሪደሃር፤ ሰመራ፣ ዱብቲ እና ኤሊዳር የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow there will be better cloud cover over the North-West, North-East, West, South-West and South areas of our country. In addition to this, from South Wolo Zone of Amhara Region; Asosa and Mao Komo zones of Benshangul Gumuz region; Kelem, West and East Wolega, Ilubabor, Buno Bedele, Jimma, Guji and West Arsi zones of Oromia region; Kefa and Sheka zones of South West Ethiopia region and Sidama region zones will get light amount of rain.. On the other hand, in Gambella, Abobo, Funedo Asosa, Bullen, Metema; Quara, Kamashi, Gode, Semera. Dubti and Elidar numerical forecast data indicates that the maximum temperature of the day will be above 35°C.