Daily Weather Report 25 Feb 25
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ ትግራይ፣ ምዕራብ አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ምዕራብ ኦሮሚያ፣ ጋምቤላ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በአንዳንድ አከባቢዎቻቸው ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ በፉኚዶ፣ በገዋኔ እና በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ38°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover over some areas of western Tigray, west Amhara, Benishangul-Gumuz, west Oromia, Gambella and southwestern Ethiopia. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded above 38°C in Gambella, Fugnido, Gewane and Gode.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል። በሌላ በኩል በምዕራብ ትግራይ፣ ምዕራብ አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በጥቂት የደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢዎች፣ በአፋር እና በደቡብ ሶማሌ ዝቅተኛ ቦታዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, there will be occasional cloud cover over the northwest, west, southwest and southern parts of our country. On the other hand, our numerical forecast indicates that the maximum temperature for the day will exceed 35°C in the low lands of western Tigray, west Amhara, Benishangul-Gumuz, Gambella, a few areas of southern Ethiopia, Afar and southern Somali.