Daily Weather Report 25 Feb 24
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ሳሳ ያለ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ በሌላ በኩል በመተማ፣ በፓዌ፣ በሸርኮሌ፣ በጋምቤላ፣ በፉኚዶ፣ በሰመራ፣ በአዋሽ አርባ፣ በቴፕ፣ በሳዉላ፣ በምዕራብ አባያ፣ በቀብሪዳሃር እና በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, scattered cloud coverage was observed over the western, southwestern, and northeastern portions of the country. Conversely, the maximum temperature of the day exceeded 35°C in Metema, Pawe, Sherkole, Gambella, Fugnido, Samara, Awash Arba, Tepi, Sawula, Mirab Abaya, Kebridahar and Gode.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በአንዳንድ የምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ እና ከፋ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ የማግኘት እድል ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ ትግራይ፣ በምዕራብ አማራ፣ በደቡብ አፋር፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጥቂት አከባቢዎች እና በደቡብ ሶማሌ ዝቅተኛ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
For the upcoming day, some areas in the western, southwestern, and northwestern portions of our country are expected to have cloud coverage. As a result, there will be a chance of light rain in a few areas of the Sheka and Kefa zones of the southwest Ethiopian region. In contrast, numerical forecast information depicts that the maximum temperature of the day will exceed 35°C in lowland areas of western Tigray, western Amhara, south Afar, Benishangul Gumuz, Gambella, a few parts of the south Ethiopian region, and south Somali.