Daily Weather Report 25 Feb 22
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደንግላ እና በጎሬ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ በፉኚዶ፣ በላሬ፣ በቴፒ፣ በተርጫ፣ በአርባ ምንጭ፣ በምዕራብ አበያ፣ በቢለቴ፣ በኮንሶ፣ በመተሓራ እና በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud coverage was observed over the western, southwest, and north parts of the country. In line with this, in Dangila and Gore light rainfall was recorded. However, the maximum temperature of the day was recorded exceeding 35°C in Gambella, Fugnido, Lare, Tepi, Terca, Arba Minch, Mirab Abaya, Bilate, Konso, Matahera and Gode.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ ትግራይ፣ በምዕራብ አማራ፣ በሰሜን አፋር፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በጥቂት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እና በደቡብ ሶማሌ ዝቅተኛ ቦታዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
For the next day, there will be occasional cloud coverage over the western, southwestern, and north parts of the country. However, the maximum daily temperature will be above 35°C in western Tigray, western Amhara, north Afar, Benishangul Gumuz, Gambella, some parts of southern Ethiopia region, and southern Somali.