Daily Weather Report 25 Feb 21

Weather Summary for previous day

Feb. 20, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአዲግራት፣ በስንቃጣ፣ በደብረታቦር፣ በዳንግላ እና በጎሬ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ በፉኚዶ፣ በፓዌ፣ በሸርኮሌ፣ በሰመራ፣ በገዋኔ፣ በአዋሽ አርባ፣ በመተሀራ፣ በተርጫ፣ በሳዉላ፣ በምዕራብ አባያ፣ በቀብሪዳሃር እና በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud coverage was observed over the northeastern, northwestern, and western parts of the country. As a result, in Adigrat, Senkata, Debretabor, Dangil, and Gore light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded. In contrast, the maximum temperature of the day was recorded exceeding 35°C in Gambella, Fugnido, Pawe, Sherkole, Semera, Gewane, Awash Arba, Metehara, Tercha, Sawula, Mirab Abaya, Kebridahar and Gode.

Weather Forecast for next day

Feb. 22, 2025

በነገው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ ትግራይ፣ በምዕራብ አማራ፣ በደቡብ አፋር፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በጥቂት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል እና በደቡብ ሶማሌ ዝቅተኛ ቦታዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

For the next day, there will be occasional cloud coverage over the western, southwestern, and northwestern portions of the country. However, the numerical forecast information shows that the maximum temperature of the day will be above 35°C in lowland areas of western Tigray, western Amhara, southern Afar, Benishangul Gumuz, Gambella, some parts of southern Ethiopia region, and southern Somali.