Daily Weather Report 25 Feb 20

Weather Summary for previous day

Feb. 19, 2025

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በጋቲራ እና ጭራ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ በጋምቤላ እና በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ40°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, they had cloud cover over the western parts of the country. Along with this, light rainfall was recorded in Gatira and Chira. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded above 40°C in Fugnido, Gambella and Gode.

Weather Forecast for next day

Feb. 21, 2025

በነገው ዕለት በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምስራቅ እና ደቡብ ምስራቅ፤ ከአማራ ክልል የደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብ ጎጃም እና ዋግህምራ፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ አማራ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ በጋምቤላ እና በደቡብ ሶማሌ አከባቢዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover over the north, northwest, west and southwestern parts of our country. In line with this, from Tigray region east and southeast; from Amhara region south Gondar, west Gojjam and Waghmra; from Oromia region Jimma, Ilubabor, west and Kelem Welega zones will receive light amount of rain in a few places. On the other hand, our numerical weather forecast information indicates that the maximum temperature of the day will exceed 35°C in west Amara, Benishangul Gumuz region, Gambella and south Somalia.