Daily Weather Report 25 Feb 19

Weather Summary for previous day

Feb. 18, 2025

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አማራ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በምዕራብ ኦሮሚያ እና በጋምቤላ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በደባርቅ፣ በአይከል፣ በጎንደር፣ በፓዌ፣ በጋቲራ፣ በጋምቤላ፣ በላሬ እና በፉኝዶ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ በፉኝዶ፣ እና በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ40°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, they had cloud cover in west Amara, Benshangul Gumuz, west Oromia and Gambella. Along with this, light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded in Debarak, Aykel, Gondar, Pawe, Gatira, Gambella, Lare and Fugnido. On the other hand, in Gambella, Fugnido, and Gode, the maximum temperature of the day was recorded above 40°C.

Weather Forecast for next day

Feb. 20, 2025

በነገው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተየያዘም ከኦሮሚያ ክልል የጅማ እና ኢሉባቦር፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ እና ሸካ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በምዕራብ አማራ እና በደቡብ ሶማሌ አከባቢዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚሆን አሀዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover over the western, southwestern and northern parts of our country. In line with this, from the Oromia region Jimma and Ilubabor; from southwestern Ethiopia region Kefa and Sheka zones receive light rainfall in a few places. On the other hand, our numerical forecast indicates that in the areas of Gambella, Benishangul Gumuz, west Amara and south Somali the maximum temperature of the day will exceed 35°C.