Daily Weather Report 25 Feb 18
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በምዕራብ እና በደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የምስራቅ ትግራይ ዞን፤ የሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ የኢሉባቦር፣ ጅማ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ የጋምቤላ ክልል ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ ዞን እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በፉኝዶ፣ በጋምቤላ እና በጎዴ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ40°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, they had cloud cover over the north east, central, west and south parts of the country. Along with this, the east Tigray zone; north, central and south Gondar, Awi zone, north and south Wolo zones; Ilubabor, Jimma, west and east Welga and west Shewa zones; Gambella region zones from Southwest Ethiopia region Sheka zone and Sidama region zones was recorded light to moderate (1-29 mm) amount of rainfall. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded above 40°C in Fugnido, Gambella and Gode.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከአማራ ክልል የአዊ ዞን፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል እና አሶሳ ዞኖች፣ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ እና ቄለም ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የከፋ ዞን በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በምዕራብ አማራ፣ በጋምቤላ እና በደቡብ ሶማሌ አከባቢዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover over the northwest, west and southwest parts of our country. In association with this, from Amhara region Awi zone; from Benshangul Gumuz region Metekel and Assosa zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, west and Kelem Welega zones; from southwest Ethiopia region Kefa zone will receives a light amount of rain in a few places. On the other hand, our numerical forecast indicates that the maximum temperature of the day will be above 35°C in west Amara, Gambella and South Somali.