Daily Weather Report 25 Feb 17

Weather Summary for previous day

Feb. 16, 2025

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ አጋማሽ፣ በደቡብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተስፋፋ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ የሰሜንና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ዋግኸምራ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ የኢሉባቦር፣ ጅማ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ጉጂ እና ሰሜን ሸዋ (ሰላሌ) ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ ዞን፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞን እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, widespread cloud coverage was observed over the western half, southern, north eastern, and central areas of the country. Consequently, in the south eastern and eastern Tigray zones; north and south Gondar, west and east Gojjam, Awi zone, north and south Wollo, Waghemra, and north Shewa zones; Ilubabor, Jimma, west and east Wellega, west Guji and north Shewa (Salale) zones; from the south west Ethiopia region Sheka zone; from the central Ethiopia region Gurage zone and Sidama region zones light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded.

Weather Forecast for next day

Feb. 18, 2025

በነገው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በቄለም፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ኢሉባቦር፣ ጅማ፣ ቡኖ በደሌ፣ ሸካ እና ከፋ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በምዕራብ አማራ፣ በደቡብ አፋር እና በደቡብ ሶማሌ ዝቅተኛ ቦታዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

For the next day, the west, southwest, and northwest portions of the country will have cloud coverage. In this regard, there will be light rain at a few places of Kelam, west Wellega, Ilubabor, Jimma, Buno Bedele, Sheka, and Kefa zones. Conversely, the forecast information shows that the maximum temperature of the day will be exceeding 35°C in the lowland areas of Benishangul Gumuz, Gambella, west Amhara, south Afar, and south Somali.