Daily Weather Report 25 Feb 16

Weather Summary for previous day

Feb. 15, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን፣ በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በመቀሌ፣ በደባርቅ፣ በጎንደር፣ በዳንግላ፣ በባህርዳር፣ በላሊበላ፣ በነፋስመዉጫ፣ በሲሪንቃ፣ በደብረወርቅ፣ በፍቼ፣ በአምቦ እና በበደሌ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ 40.2፣ በተርጫ 35.2፣ በሳዉላ 36.5፣ በአርባ ምንጭ 35.8፣ በብላቴ 35.8፣ በኮንሶ 35.0፣ በመተሀራ 36.4 እና በጎዴ 40.8 የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, the country's north, west, southwest, and central parts experienced better cloud coverage. In this regard, light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded in Mekelle, Debark, Gondar, Dangila, Bahirdar, Lalibela, Nefasmewcha, Sirinka, Debrework, Fiche, Ambo and Bedele. Conversely, the maximum temperature of the day was recorded above 35°C in Gambella 40.2, Tercha 35.2, Sawula 36.5, Arba Minch 35.8, Bilate 35.8, Konso 35.0, Metehara 36.4 and Gode 40.8.

Weather Forecast for next day

Feb. 17, 2025

በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከአማራ ክልል የማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን እና ምዕራብ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ቄለም እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የማኦኮሞ ዞን፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች እና ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ እና ከፋ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በምዕራብ አማራ፣ በደቡብ አፋር እና በደቡብ ሶማሌ ዝቅተኛ ቦታዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

For the upcoming day, there will be cloud coverage over our country's northwest, northeast, central, western, and southwest areas. Besides, from Amhara region the central and south Gondar, Awi zone, and west Gojjam zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, Kelam, and west Wellega zones; from Benishangul Gumuz region Mao Komo zone; from Gambella region Agnuak and Majang zones and the southwest Ethiopia region Sheka and Kefa zones will experience light rain at a few places. On the other hand, numerical forecast data indicates that the maximum temperature of the day will be above 35°C in lowland areas of Gambella, Benishangul Gumuz, west Amhara, south Afar, and south Somali.