Daily Weather Report 25 Feb 15

Weather Summary for previous day

Feb. 14, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ ምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደባርቅ፣ በዳንግላ፣ በአሶሳ፣ በበደሌ እና በጎሬ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ 40.2፣ በቴፕ 37.6፣ በተርጫ 35.2፣ በአማን 35.0፣ በሳዉላ 36.0፣ በአርባ ምንጭ 36.5፣ በብላቴ 36.0፣ በኮንሶ 35.5፣ በመተሀራ 36.0 እና በጎዴ 41.0 የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud coverage was observed over the northwest, west, southwest, and northeast parts of the country. In this regard, in Debark, Dangila, Asossa, Bedel,e and Gore light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded. In contrast, the maximum temperature of the day was recorded above 35°C in Gambella 40.2, Tepi 37.6, Tercha 35.2, Aman 35.0, Sawula 36.0, Arba Minch 36.5, Bilate 36.0, Konso 35.5 and Gode 41.0.

Weather Forecast for next day

Feb. 16, 2025

በነገው ዕለት በምዕራብ አጋማሽ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኸምራ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ ሸዋ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ዞን፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ ዞን፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ እና ከፋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በደቡብና ሰሜን አፋር፣ በምዕራብ አማራ እና በደቡብ ሶማሌ ዝቅተኛ ቦታዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎቻችን ያመላክታሉ፡፡

Tomorrow, our country's western half, northeastern, central, and southern portions will have better cloud coverage. Along with this, from the Tigray region the northwest, central and southeastern zones; from the Amhara region the north, central, and south Gondar, west and east Gojjam, Waghemra, and north Wollo zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega, Buno Bedele, west Shewa, and west Arsi zones; from Benishangul Gumuz region Asossa zone; from Gambella region Agnuak zone; from the southwest Ethiopia region Sheka and Kefa zones; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Hadiya, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones and the Sidama region zones will experience light to moderate rainfall. Conversely, our forecast information indicates that the daily maximum temperature will exceed 35°C in lowlands areas of Gambella, Benishangul Gumuz, south and north Afar, west Amhara, and south Somali.