Daily Weather Report 25 Feb 14

Weather Summary for previous day

Feb. 13, 2025

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በሰሜን ምዕራብ እና በሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ በሌላ በኩል በመተማ 42.2፣ በገዋኔ 37.2፣ በአዋሽ አርባ 36.2፣ በጋምቤላ 40.6፣ በቴፕ 37.4፣ በተርጫ 36.0፣ በአማን 35.0፣ በሳዉላ 36.0፣ በአርባ ምንጭ 36.5፣ በምዕራብአባያ 36.5፣ በብላቴ 36.3 እና በጎዴ 41.0 የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, cloud coverage was noted over the western, southwestern, northwestern, and northeastern parts of the country. Meanwhile, the maximum temperature of the day was recorded above 35°C in Metema 42.2, Gewane 37.2, Awash Arba 36.2, Gambella 40.6, Tepi 37.4, Tercha 36.0, Aman 35.0, Sawula 36.0, Arba Minch 36.5, Mirab Abaya 36.5, Bilate 36.3 and Gode 41.0.

Weather Forecast for next day

Feb. 15, 2025

በነገው ዕለት በምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በሰሜን፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ አዊ ዞን፣ ዋግኸምራ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቄለም፣ ሆሮ ጉዱሩ፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ፣ ቡኖ በደሌ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል፣ አሶሳ እና ማኦ ኮሞ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ እና ከፋ ዞኖች በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በምዕራብ አማራ እና በደቡብ ሶማሌ ዝቅተኛ ቦታዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡

For the upcoming day, the west, southwest, north, central, and east portions of our country will have cloud coverage. Consequently, from Tigray region the west, northwest, central, and southeast zones; from Amhara region the west, north, central and south Gondar, west and east Gojjam, Awi zone, Waghemra, and north Wollo zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, Kelam, Horo Guduru, west and east Wellega, Buno Bedel,e and west Shewa zones; from Benishangul Gumuz region Metekal, Asossa and Mao Komo zones and the southwest Ethiopia region Sheka and Kefa zones of will receive light rainfall at some places. Conversely, our forecast information shows that the daily maximum temperature will exceed 35°C in lowland areas of Gambella, Benishangul Gumuz, west Amhara, and south Somali.