Daily Weather Report 25 Feb 13

Weather Summary for previous day

Feb. 12, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በምዕራብ ትግራይ፣ በምዕራብ አማራ እና በምዕራብ ኦሮሚያ የተሻለ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሽሬ፣ በደባርቅ፣ በነጆ፣ በአንገርጉትን፣ በአይራ፣ በአርጆ እና በቡሬ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ፣ በአፋር፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በደቡብ ሶማሌ ቆላማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ 35°C በላይ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was better cloud cover over the west Tigray, west Amara, and west Oromia. In association with this, a light amount of rainfall was recorded in Shire, Debarak, Nejo, Angergutin, Aira, Arjo, and Bure. On the other hand, the maximum temperature of the day was recorded above 35°C in the lowlands of Gambella, Benishangul Gumuz, Afar, South Ethiopia, and South Somalia.

Weather Forecast for next day

Feb. 14, 2025

በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብና ሰሜን ምዕራብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል ሰሜንና ደቡብ ጎንደር ዞኖች፣ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ምዕራብ ወለጋ እና ኢሉባቦር ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ እና ከፋ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በምዕራብ አማራ እና በደቡብ ሶማሌ ዝቅተኛ ቦታዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከ35°C በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover over the northwest, northeast, west and southwestern parts of our country. Along with this, the western and northwestern zones of the Tigray region; From Amhara region north and south Gondar zones; from Oromia region Jimma, west Wellega and Ilubabor zones; from southwestern Ethiopia Sheka and Kefa zones will receive light rainfall in a few places. On the other hand, our forecast information indicates that the maximum temperature of the day will be above 35°C in the lowlands of Gambella, Benishangul Gumuz, west Amara and South Somali.