Daily Weather Report 25 Feb 12
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም የማዕከላዊ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ የደቡብ ጎንደር እና ሰሜን ወሎ ዞኖች፤ የኢሉባቦር፣ ቄለም፣ ምዕራብና ምስራቅ ወለጋ እና ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ኑዌር ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ ዞን እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud coverage was observed over the northeastern, southwestern, and central parts of the country. As a result, in the central, southeast, and east Tigray zones; south Gondar and north Wollo zones; Ilubabor, Kelam, west and east Wellega, and west Shewa zones; Agnuak and Nuwer zones of the Gambella region; the Sheka zone of the southwest Ethiopia region; and the Sidama region zones, light to moderate (1-29 mm) rainfall was recorded.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ አጋማሽ፣ በደቡብ፣ በሰሜን ምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን፣ ማዕከላዊና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖ በደሌ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ከፋ፣ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች፣ ከጋምቤላ ክልል የማጃንግ ዞን፣ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በጥቂት መተከል እና ካማሽ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
For the next day, the western half, south, northeast, and central parts of our country will have cloud coverage. Along with this, from the Tigray region, the west, northwest, central, and eastern zones; from the Amhara region, the northern, central, and southern Gondar, Awi zone, western and eastern Gojam zones; from the Oromia region, Jimma, Ilubabor, Buno Bedele, western and eastern Wellega zones; from the southwest Ethiopia region, Sheka, Kefa, and Bench Sheko zones; from the Gambella region, the Majang zone; and from the Benishangul Gumuz region, with a few Metekel and Kamashi zones, will receive light rainfall.