Daily Weather Report 25 Feb 11
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በምዕራብና ደቡብ ኦሮሚያ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና በሲዳማ የተሻለ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በኢጃጂ፣ በበደሌ፣ በጋቲራ፣ በጭራ፣ በጎሬ፣ በቁልምሳ፣ በሀዋሳ፣ በእምድብር፣ በሆሳዕና እና በወራቤ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was better cloud cover across the western and southern Oromia, central Ethiopia, and Sidama. In association with this, light to moderate (1-29 mm) amounts of rainfall were recorded in Ejaji, Bedele, Gatira, Gore, Kulumsa, Hawassa, Emdibir, Hosanna and Werabe.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በደቡብ ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያሳያሉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከትግራይ ክልል የምዕራብ፣ ማዕከላዊ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ደቡብ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል ሰሜን፣ ማዕከላዊ እና ደቡብ ጎንደር፣ አዊ ዞን፣ ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፣ ከአፋር ክልል የቅልበቲ ዞን፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ምዕራብ አርሲ እና ባሌ ዞኖች፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ዳውሮ እና ከፋ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡
Tomorrow, our forecast information shows that there will be cloud cover in the northwest, southwest, northeast, south, and eastern parts of our country. In line with this, from the Tigray region west, central, southeast, and south zones; from the Amhara region north, central, and south Gonder; Awi zone, west and east of Gojjam, Waghemra, North Shewa, North and South Wollo zones, Afar region Kilbeti zone; from the Oromia region Jimma, west Arsi, and Bale zones; from the Southwest Ethiopia region Sheka, Dauro, and Kefa zones; from the south Ethiopian region Welayta, Gofa, and Gedeo zones; and the zones of the Sidama region will receive light to moderate (1-29 mm) amounts of rainfall.