Daily Weather Report 25 Feb 09
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጪራ እና በቴፒ ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል የተቀሩት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ፀሃያማና ሞቃታማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡
Yesterday was chance cloud coverage in the west, central and southwest parts of the country. In line with this, light rain was recorded over Cira and Teppi. However, the rest of the country is experiencing sunny and warm weather conditions.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ ፣ ምዕራብ ና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች ፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከፋ፣ሸካ አና ኮንታ ዞኖች እና ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀድያ፣ የየም ልዩ ዞን እና ከምበታ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ የትንበያ መረጃዎቻችን ያሳያሉ፡፡ በሌላ በኩል የታቀሩት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ፀሃያማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow, there will be cloud coverage in the west, central, south and southwest of parts of the country. In line with this, from Oromia region Jimma, east and west Harerge and zones and from the Southwest Ethiopia region Kefa, Sheka and Konta zones and from central Ethiopia region Hadiya, and Yem special zone will receive light rainfall. On the other hand, the rest of the country will dominate under sunny weather condition.