Daily Weather Report 25 Feb 08
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገራችን ክፍሎች ላይ ፀሃያማና ሞቃታማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡
Yesterday, sunny and warm weather was observed in the northeast, northwest, central, southeast and eastern parts of our country. On the other hand, there was occasional cloud coverage in the south, southwest and west parts of the country.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ ፣በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን ክፍሎች የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች ፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከፋ፣ሸካ አና ኮንታ ዞኖች እና ከአፋር ክልል ቂልበቲ ዞን ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያሳያሉ፡፡ በሌላ በኩል የታቀሩት የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ፀሃያማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow, there will be cloud coverage in the northeast, west, central, east, south and southwest of parts of the country. In line with this, our numerical weather forecasting information shows that the zones of Sidama region; from Oromia region Jimma and west Arsi zones and from the South west Ethiopia region Kefa, Sheka and Konta zones and from Afar region Kilbet zone will receive light rainfall. On the other hand, the rest of the country will dominate under sunny weather condition.