Daily Weather Report 25 Feb 07
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በሰሜን ምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገራችን ክፍሎች ላይ ፀሃያማና ሞቃታማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡
Yesterday, sunny and warm weather was observed in the northeast, northwest, central and eastern parts of our country. On the other hand, there was occasional cloud coverage in the south, southwest and west parts of the country.
Weather Forecast for next day
በነገዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ ፣በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በምስራቅ፣ በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል ጅማ ዞን እና ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ከፋ ዞን ቀላል መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያሳያሉ፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ፀሃያማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow, there will be cloud coverage in the northeast, west, central, east, south and southwest of Ethiopia. In connection with this, our numerical weather forecasting information shows that the zones of Sidama region; from Oromia region Jimma zone and from the South west Ethiopia region Kaffa zone will receive light rainfall. On the other hand, there will be sunny weather in the northwest areas of our country.