Daily Weather Report 25 Feb 04

Weather Summary for previous day

Feb. 3, 2025

በትናንትናው ዕለት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ አመዝኖባቸው ውሏል፡፡ ይሁን እንጂ በደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡

Yesterday, dry, sunny, and windy weather prevailed in most parts of the country. However, cloud coverage was observed over the southwestern and southern areas.

Weather Forecast for next day

Feb. 5, 2025

በነገው ዕለት በሰሜን ምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ሊመዘገብ እንደሚችል አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብና ደቡብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, the northwest, northeast, central, southern highlands, and eastern portions of the country will have dry, sunny, and windy weather. In association with this, numerical forecast information indicates that the minimum temperature of the day may be recorded below 5°C. Conversely, cloud coverage will be noticeable in the southwest and southern parts of our country.