Daily Weather Report 25 Feb 03
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በወገልጤና 4.8፣ በአምባማሪያም 4.8፣ በሾላገበያ 4.0፣ በቡኢ 4.0 እና በጅግጅጋ 4.6 የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5oC በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ይሁን እንጂ በደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በጭራ እና በአማን ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል::
Yesterday, the Bega dry, sunny, and windy weather was observed over the northeast, central, and east parts of the country. As a result, the daily minimum temperature dropped below 5°C in Wegeltena 4.8, Ambamariam 4.8, Sholagebeya 4.0, Bui 4.0 and Jigjiga 4.6. However, cloud coverage was observed over the southwestern and southern parts of the country. In this regard, light rain was recorded in Chira and Aman.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በአብዛኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ ይስተዋላል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በጥቂት የምስራቅ አማራ፣ መካከለኛው፣ ደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና ምስራቅ ኦሮሚያ ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ሊመዘገብ እንደሚችል የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ ምዕራብና በደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡
For the upcoming day, the Bega dry, sunny, and windy weather will be observed in most parts of our country. Consequently, the forecast information indicates that the day’s minimum temperature may drop below 5°C in a few areas of east Amhara, central, southern highlands, and east Oromia region. On the other hand, southwest and southern parts of the country will have cloud coverage.