Daily Weather Report 25 Feb 01

Weather Summary for previous day

Jan. 31, 2025

በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በደቡብ፣ በመካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና የነበራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘም በቴፒ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል::

Yesterday, the dry, sunny and windy weather of bega was observed in the North-East, South, Central and East regions of the country. However, there were clouds over the southwestern parts of the country and light rainfall was recorded in Tepi.

Weather Forecast for next day

Feb. 2, 2025

በነገው ዕለት በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን በጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሸካ እና ቤንች ሸኮ ዞኖች በጥቂት ስፍራዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የበጋው ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ እንደሚስተዋልባቸዉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow, there will be cloud cover in the southwest areas of our country and there will be light rain at some places in Jimma, Ilubabor, Sheka and Bench Sheko zones. On the other hand, numerical forecasts indicate that sunny and windy bega weather will be observed in the north, central, northeast and eastern parts of the country.