Daily Weather Report 25 December 31
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በደቡብ፣ በምስራቅ፣ በደቡብምዕራብና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሻምቡ፣ ፉኚዶ፣ ሳዉላ ፣ ጂንካ፣ አርባምንጭ፣ ምራብ አባያ፣ ኮንሶ፣ ያቤሎ፣ ዲላ፣ ቦሬ፣ዲሜካ፣ ኮበን፣ ኦንጋ እና ይርጋለም ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በቡርኪ 24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በኮሶበር፣ በአምባ ማርያም፣ ወገልጤና፣ ጋሸና፣ ዳንግላ፣ ግናገር፣ በጨለንቆ እና በቁሉቢ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover in the southern, eastern, southwest, and western parts of our country. As a result, light to moderate rainfall (1-29 mm) was recorded in Shambu, Fugnido, Sawla, Jinka, Arbaminch, Mirababaya, Konso, Yabelo, Dilla, Bore, Dimeka, Koben, Onga, and Yirgalem. Additionally, heavy rainfall exceeding 30 mm was recorded in Bulki within 24 hours. On the other hand, the northeast, central, and eastern regions of our country experienced dry, sunny, and windy Bega weather. In this regards, in Kosober, Amba Mariam, Wegeltena, Gashena, Dangla, Ginager, Chelenko, and Kulubi, the daily minimum temperature was recorded below 5 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ አርሲ፣ሰሜን እና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖች፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የደቡብ ዞን በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡
Tomorrow there will be cloud cover in the southern parts of the country, which are experiencing the second rainy season of Bega, as well as in the southwest, west, central, and northeastern parts of the country. In association this, from southern Ethiopia region Wolaita, Gofa, Basketo, and Gedeo zones; Sidama region zones; from Oromia region Guji and West Guji, Bale, and West Arsi zones will receive light to moderate rainfall (1-29 mm) amount of rainfall. Additionally, from Southwest Ethiopia region Sheka, Bench Sheko, Kefa, Konta, West Omo, and Dawro zones; from Oromia region, Jimma, Arsi, North and Southwest Shewa zones; from the Central Ethiopian region Gurage, Silte, Hadiya, Halaba, Yabelo Special Zone, Kembata and Tembaro zones; from Amhara region North Shewa, North and South Wollo zones; and in the Southern Zone of Tigray region there will be light unseasonal rain in a few places. On the other hand, the northern and eastern parts of the country will experience dry, sunny, and windy Bega weather conditions.