Daily Weather Report 25 December 30
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በያቤሎ፣ ቡሌሆራ፣ ቡርጅ፣ ጂንካ፣ ሳዉላ፣ ዲላ፣ አርባ ምንጭ፣ ተርጫ፣ ቴፒ፣ ወሊሶ፣ አንጋጫ፣ ወልቂጤ፣ ዲመካ፣ አዲስ አለም፣ አሺ እና ኦሞናዳ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ በጥቂት የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud coverage was observed over the southern, southwestern, and central parts of the country. In this regard, light to moderate rainfall was recorded in Yabelo, Bulehora, Burji, Jinka, Sawula, Dilla, Arba Minch, Tercha, Tepi, Woliso, Angacha, Welkite, Dimeka, Addis Alem, Ashi and Omo Nada. Conversely, dry, sunny and windy Bega weather condition was observed in the northwest, northeast and east of the country. In a few highland areas, the day’s minimum temperature was recorded below 5 degrees Celsius.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ፣ ሊበን እና ሸበሌ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ ዞን እና ከሶማሌ ክልል የፋፈን እና ጃራር ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
For the upcoming day, better cloud coverage is expected over the south and south eastern parts of our country, which are in their second rainy season of the Bega. Associated with this, from the south Ethiopian region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, south Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji, and Gedeo zones; Sidama region zones; from Oromia region the Guji and west Guji, Borena and east Borena, Bale and west Arsi zones, and from Somali region the Dawa, Liben and Shebelle zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall. Besides, due to the strengthening rain-bearing weather events, from the south west Ethiopian region Bench Sheko, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from Oromia region Jimma, west, north, south west and east Shewa, Arsi, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from central Ethiopia region Gurage, Silte, east Gurage, Kebena special zone, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from Amhara region west Gojjam, north Shewa, north and south Wollo zones; from Tigray region south, south east and east zones; from Afar region Kilbeti zone and of Somali region Fafen and Jarar zones will experience light unseasonal rainfall at a few places.