Daily Weather Report 25 December 29
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በደቡብ፣ በደቡብምዕራብና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በጂማ፣ ጂንካ፣ ሳዉላ ፣ ቴፒ፣ ቡርጂ፣ ያቤሎ፣ ሀዋሳ፣ ቢላቴ፣ ዲላ፣ ሶኮሩ፣ ሆሳዕና፣ ወላይታ ሶዶ፣ ምራብ አባያ፣ ቡሌሆራ፣ ሆሞናዳ፣ ይርጋለም፣ ዲሜካ፣ አማን እና ወንዶ ገነት ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በአርባምንጭ 24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በበኮረም፣ በኮሶበር፣ በጋሸና እና በጨለንቆ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday there were cloudy skies over the southern, southwestern, and western parts of our country. In connection with this, light to moderate rainfall (1–29M.M) was recorded in Jimma, Jinka, Sawula, Teppi,Burji,Yabelo,Hawassa,Bilate,Dilla,Sokoru,Hosana,Wolayta Sodo,Mirab Abaya,Bulehora,Homona Dada,Yirgalem,Dimeka,Aman, and Wondo Genet. In addition, heavy rainfall exceeding 30M.M was recorded at Arba Minch within 24 hours. Meanwhile, the northern, northeastern, central, and eastern parts of the country experienced dry, sunny, and windy conditions. Correspondingly, low daytime temperatures below 5°C were recorded in korem, Kosober, Gashena, and Chelenko.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ፣ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በደቡብ ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ አርሲ እና ቦረና ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን(1-29 ሚ.ሜ) ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የጅማ፣ አርሲ፣ ሰሜን፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ዳዉሮ ዞን፤ የጉራጌ፣ ቀቤና ልዩ ዞን፣ ማረቆ ልዩ ዞን ፣ የም ልዩ ዞን፣ ስልጤ፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የደቡብ ምስራቅ፣ ደቡብ እና ምስራቅ ትግራይ ዞኖች፤ የሰሜንና ደቡብ ወሎ፣የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቂልበቲ፣ ሀሪ እና ፋንቲ ዞኖች በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን እና በምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡
Tomorrow during the main rainy season there will be cloudy patches over parts of the country in the south, south‑east, west, north‑east, central and south‑west. In connection with this, light to moderate rainfall (1–29M.M) is expected in some areas of Oromia Gujii and West Gujii, West Arsi and Borena zones; Southern Ethiopia Region Wolayita,Gamo,Gofa,Basketo,South Omo, Gardula,Kore,Ale,Konso,Burji and Gedeo zones; and Zones of Sidama region. In addition, unseasonal light rain is expected in some places of the following zones: Jimma, Arsi, North, West, South‑West and East Shewa zones; Addis Ababa; Dawuro zone; Gurage,Kebena and special zones,Mareko special zone,Yem special zone,Silte,Halaba,Hadiya,Kembata and Tambaro zones; South‑East, South and East Tigray zones; North and South Wollo,the Oromo special zone and North Shewa zones; and from Afar region Kilbet, Hari and Fanti zones. Elsewhere across the northern and eastern parts of the country, dry, sunny and windy weather will prevail.