Daily Weather Report 25 December 28
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በኮንሶ፣ ቡርጅ፣ ጂንካ፣ ሳዉላ እና ሆሳዕና ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ በጥቂት የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud coverage was observed over the south, south west and central parts of country. Consequently, Konso, Burji, Jinka, Sawula and Hosaina received light to moderate (1-29 mm) rain. In contrast, the dry, sunny and windy weather of the Bega season was observed in the north west, north east and eastern parts of the country, with the minimum temperature of the day was recorded below 5 degrees Celsius in a few highlands of the country.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮንሶ፣ አሌ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል በጥቂት የቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ፣ ምዕራብ አርሲና አርሲ፣ ጅማ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች እና ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር የሚስተዋል ሲሆን፤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ እንደሚመዘገብ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማል፡፡
Tomorrow, the south which is in their second rainy season of the Bega, as well as, southwestern, western and central parts of the country will have cloud coverage. Associated with this, from the south Ethiopian region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, south Omo, Gardula, Konso, Ale and Gedeo zones; Sidama region zones; Oromia region in some areas of Borena, Guji and west Guji, Bale, west Arsi and Arsi, Jimma, southwest and east Shewa zones; from the south west Ethiopian region west Omo and Dawuro zones, and from the central Ethiopian region Gurage, Silte, Kebena special zone, east Gurage, Mareko special zone, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones will have light rainfall at a few places. On the other hand, the northwest, northeast, and eastern parts of the country will experience dry, sunny, and windy Bega weather conditions; with the forecast information’s indicate that the daily minimum temperatures expected to drop below 5°C.