Daily Weather Report 25 December 27

Weather Summary for previous day

Dec. 26, 2025

በትናንትናው ዕለት የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በሰሜን፣ በሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በጥቂት የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በጥቂት የደቡብ ምዕራብ፣ ደቡብ እና መካከለኛው የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው ሲሆን በወሊሶ እና እምድብር ቀላል መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡

Yesterday, the dry, sunny, and windy Bega weather was observed in the north, north west, north east, and east parts of the country. Along with this, the minimum temperature of the day was recorded below 5 degree Celsius in some highland areas of the country. On the other hand, in a few areas of the south west, south, and central parts of the country, had cloud coverage, with Waliso and Emdibir receiving light rainfall.

Weather Forecast for next day

Dec. 28, 2025

በነገው ዕለት በሰሜን፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ሰሜን ምስራቅ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በአንዳንድ የምስራቅ አማራ፣ መካከለኛው፣ ደቡብ ከፍተኛ ቦታዎች እና ምስራቅ ኦሮሚያ ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛው የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን የሚኖራቸው ሲሆን፤ የምስራቅ ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ሀድያ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ከምባታ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጌድኦ እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, the north, northwest, northeast, and east parts of the country will experience dry, sunny, and windy Bega weather conditions. In this regard, the forecast indicates that the minimum temperature of the day will be recorded below 5 degrees Celsius in some areas of east Amhara, central, south highlands, and east Oromia region. Conversely, there will be cloud coverage in the south, south west, and central portions of our country; accordingly, east Gurage, Silte, Hadiya, Mareko special zone, Halaba, Kembata, Arsi, and west Arsi, Bale, Guji, and west Guji, Walaita, Gamo, Gede,o and Sidama region zones will have light to moderate (1-29 mm) rainfall at a few places.