Daily Weather Report 25 December 26

Weather Summary for previous day

Dec. 25, 2025

በትናንትናው ዕለት የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ በሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው፣ ደቡብ ደጋማ ስፍራዎች እና ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በአምባማሪያም፣ ወገልጤና፣ መሀልሜዳ፣ ጋሸና፣ ዳባት፣ ኮረም፣ ቡኢ እና ባሌሮቤ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች አልፎ አልፎ የደመና ሽፋን የነበራቸው ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ፉጎሌቃ እና ሳዉላ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡

Yesterday, the dry, sunny and windy weather of the Bega season was observed in the north, north east, central, south Highlands and eastern parts of the country. In connection with this, the daily minimum temperature was recorded below 5°C in Ambamariam, Wegeltena, Mehalmeda, Gashena, Dabat, Korem, Bui, and Balerobe. In contrast, the south, south west, and west parts of the country had occasional cloud coverage, with Fugoleka and Sawula receiving light rain.

Weather Forecast for next day

Dec. 27, 2025

በነገው ዕለት በደቡብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ባሌ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ቡርጂ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮሬ እና ጌድኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚኖረው የደመና ሽፋን ላይ በመነሳት በጥቂት የጅማ፣ አርሲ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ የስልጤ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ከፋ እና ምዕራብ ኦሞ ዞኖች አነስተኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚኖራቸው ሲሆን በአንዳንድ የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

For the upcoming day, there will be cloud coverage over the southern and southwestern parts of the country. Associated with this, from Oromia region, Guji and west Guji, Bale and west Arsi zones; from the south Ethiopia region, Walaita, Gofa, Gamo, Burji, south Omo, Kore and Gedeo zones, and the Sidama region zones will receive light rain at a few places. Moreover, due to the cloud coverage, a few areas of Jimma, Arsi, south west and east Shewa zones; Silte, east Gurage, Mareko special zone, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; Bench Sheko, Kefa, and west Omo zones will experience light unseasonal rainfall. Conversely, the northern, northeastern, and eastern parts of the country will experience dry, sunny, and windy Bega weather conditions, with the forecast information indicating that the daily minimum temperatures in the highlands of the country are expected to drop below 5°C.