Daily Weather Report 25 December 25
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብና በምስራቅ ኦሮሚያ፤ በምስራቅና በመካከለኛው አማራ ፤ በጋምቤላ፤ በደቡብ ምዕራብ፣ በማዕከላዊ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በሲዳማ ክልሎች የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በይርጋለም፤ እጃጂ፣ ሊሙ ገነት፣ ሀዋሳ እና ዲላ አከባቢዎች ቀላል መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በቡኢ፣ በሐሮማያ፣ በጨለንቆ፣ በዳንግላ፣ በወገል ጤና፣ በጅግጅጋ እና በዓለም ከተማ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud coverage in the western, central, southern and eastern Oromia; eastern and central Amhara; Gambella; southwestern, central, southern Ethiopia and Sidama regions. In connection with this, light rain was received in Yirgalem; Ejaji, Limmu Genet, Hawassa and Dilla areas. On the other hand, dry, sunny and windy beg weather was observed in the north eastern, central and eastern regions of our country. In connection with this, the minimum temperature of the day was recorded below 5 degrees Celsius in Bui, Haromaya, Chelenko, Dangila, Wegel Tena, Jigjiga and Alem Ketema.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ የሀገራችን ክፍሎች እንዲሁም በምዕራብ፣ በመካከለኛ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጎፋ፣ ባስኬቶ እና ጌዳሆ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂና ጉጂ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ እና ባሌ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸዉ ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የጅማ፣ ከፋ፣ ጉራጌ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋና ከምባታ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸዉ ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋልባቸዉ ሲሆን በጥቂት ቦታዎቻቸዉ ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች ሆኖ ኢንደሚመዘገብ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎቻችን ያመለክታሉ፡፡
Tomorrow, the southern parts of our country, which are in their second rainy season of the summer, as well as the western, central and southwestern parts of the country, will have cloud coverage. In addition, the Gofa, Basketo and Gedeo zones of the Southern Ethiopia Region; Sidama Region zones, West Guji and Guji, Arsi and West Arsi and Bale zones of the Oromia Region will experience light rain at a few places. In addition, the Jimma, Kefa, Gurage, Yem special Zone, Halaba, Hadiya, Wolayta Sodo, Southwest Shewa and Kembata zones will experience light rain at a few places. On the other hand, the northeast, central, and eastern parts of the country will experience dry, sunny, and windy summer weather, with daily minimum temperatures falling below 5 degrees Celsius in some areas, according to our numerical forecast data.