Daily Weather Report 25 December 24

Weather Summary for previous day

Dec. 23, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በምስራቅና መካከለኛው አማራ፤ በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብና በምስራቅ ኦሮሚያ፤ በጋምቤላ፤ በደቡብ ምዕራብ፣ በማዕከላዊ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በሲዳማ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በመርጦለማርያም፣ ጎሬ፣ ጋቲራ፣ ጭራ፣ ጅማ፣ አቦምሳ፣ ማጅ፣ ሀዋሳ፣ ጂንካ፣ ደብረ ማርቆስ፣ ካቺሴ፣ ነቀምቴ፣ ቴፒ፣ ቢላቴ፣ አዴሌ፣ ዲላ፣ ሜረሳ፣ ቅዳሜ ገበያ፣ በኦንጋ እና በቡልኪ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በሺንዲ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በቡኢ፣ በሐሮማያ፣ በአዲግራት፣ በአምባ ማርያም፣ በኮረም፣ በጅግጅጋ እና በጨለንቆ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud coverage in East and Central Amhara; West, Central, South and East Oromia; Gambella; Southwest, Central South Ethiopia and Sidama. Along with this, light to moderate (1-29mm) rainfall was recorded in Merxolemariam, Gore, Gatira, Cira, Jimma, Abomsa, Maji, Hawassa, Jinka, Debre Markos, Kachise, Nekemte, Tepi, Bilate, Adele, Dilla, Meresa, Kidame Gebeya, Onga and Bulki. In addition, more than 30mm of heavy rainfall was recorded in Shindi in 24 hours. On the other hand, dry, sunny and windy summer weather was observed in the northeast, central and eastern parts of our country. In this regard, the daily minimum temperature was recorded below 5 degrees Celsius in Bui, Haromaya, Adigrat, Amba Mariam, Korem, Jigjiga and Chelenko.

Weather Forecast for next day

Dec. 25, 2025

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እንዲሁም በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ እና ባስኬቶ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጅ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸዉ ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የጅማ፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ከፋ፣ ጉራጌ፣ የም ልዩ ዞን፣ ሀላባ፣ ሀድያና ከምባታ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸዉ ላይ ቀላል መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ይስተዋልባቸዋል፡፡

Tomorrow, the southern, western and southwestern parts of the country, which are in their second rainy season, will have cloud coverage. In addition, the Wolayita, Gofa and Basketo zones of the Southern Ethiopian Region; Sidama Region zones, and the West Guji and West Arsi zones of the Oromia Region will experience light rain at a few places. In addition, the Jimma, Sheka, Bench Sheko, Kefa, Gurage, Yem special Zone, Halaba, Hadiya and Kembata zones will experience light rain at a few places. On the other hand, the north eastern, central and eastern parts of the country will experience dry, sunny and windy Beg weather.