Daily Weather Report 25 December 23
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በምስራቅና መካከለኛው አማራ፤ በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በደቡብና በምስረቅ ኦሮሚያ፤ በጋምቤላ፤ በደቡብምዕራብ፣ በማዕከላዊና በደቡብ ኢትዮጵያ እና በሲዳማ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸዉ፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በመካነሰላም፣ ጨፋ፣ መርሳ፣ ጉጉፍቱ፣ ደብረሲና፣ አቀስታ፣ ወግዲ፣ መንዲዳ፣ ሃራ፣ የትኖራ፣ መርጦለማርያም፣ ጎሬ፣ በደሌ፣ ጋቲራ፣ ጭራ፣ ሊሙገነት፣ ሃሮ፣ ያዮ፣ መቂ፣ ሰዲቃ፣ ቢላምቢሎ፣ ቡልቡል፣ ፉጎሌቃ፣ ጅማ፣ ሶኮሩ፣ ኢጃጅ፣ አዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ኑራኤራ፣ አቦምሳ፣ ኩልምሳ፣ አርሲሮቤ፣ ገለምሶ፣ ጃራ፣ ጊንር፣ ሲቦ፣ ትንሹሜጢ፣ አማን፣ ማጅ፣ ተርጫ፣ እምድብር፣ ሀዋሳ፣ ወልቂጤ፣ ወላይታሶዶ፣ ሳውላ፣ ጂንካ፣ አርባምንጭ እና ኮንሶ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በደብረማርቆስ፣ ብላቴ እና ቡልቂ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover and accumulation across the eastern and central Amhara; western, central, southern, and eastern Oromia; Gambella; southwestern, central, and southern Ethiopia; and Sidama. In this regard, Mekaneselam, Cheffa, Mersa, Guguftu, Debresina, Akesta, Wegdi, Mendida, Hara, Yetnora, Mertolemariam, Gore, Bedele, Gatira, Chira, Limugenet, Haro, Yayo, Meki, Sedika, Bilambilo, Bulbul, Fugoleka, Jimma, Sokoru, Ejaji, Addis Ababa, Adama, Nuraera, Abomsa, Kulumsa, Arsi Robe, Gelemso, Jara, Ginir, Sibo, Tineshumetti, Aman, Maji, Tercha, Emdibir, Hawassa, Welkite, Wolaitasodo, Sawla, Jinka, Arba Minch, and Konso received light to moderate (1-29) amounts of rainfall. Additionally, in Debre Markos, Bilatte, and Bulki, heavy rainfall exceeding 30 mm was recorded within 24 hours.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ የሀገሩቱ ክፍሎች እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛው እና በሰሜን ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሞ፣ ጎፋ፣ ባስኬቶ፣ አሪ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖበደሌ፣ ሆሮጉድሩና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ሰሜንና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ ዞኖች፤ የማዣንግና አኝዋክ ዞኖች፤ የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀቤና ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር እና ደቡብ ወሎ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover in the southern parts of the country, which are experiencing the second rainy season of Bega, as well as in the southwest, west, central, and northeastern regions of the country. In association with this, from the Southern Ethiopian region, the Wolaita, Gamo, Gofa, Basketo, Ari, and Gedeo zones; the zones of the Sidama region; and from the Oromia region, the Guji and West Guji zones will receive light rain. In addition, light to moderate rainfall (1–29 mm) is anticipated over Jimma, Ilubabor, Bunobedele, Horogudru, and East Wellega; West, North, and Southwest Shewa; Bale, Arsi, and West Arsi; Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo, and Dawuro zones; Majang and Agnuak zones; Gurage, Silte, Kebena Special Zone; Hadiya, Halaba, Yem Special Zone; Kembata and Tembaro zones; East and West Gojjam; South Gondar; and South Wollo zones.