Daily Weather Report 25 December 22
Weather Summary for previous day
በትናንትናዉ ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በደቡብ፣ በደቡብ ምዕራብና በመካከለኛው የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸዉ፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ጨፋ፣ ኮምቦልቻ፣ ስሪንቃ፣ መሃልሜዳ፣ ሀይቅ፣ ጉጉፍቱ፣ ደብረሲና፣ ከሚሴ፣ ሀርቡ፣ ወግዲ፣ ግናገር፣ ሞላሌ፣ ሀራ፣ ሮቢት፣ ካችሴ፣ ጎሬ፣ አዳማ፣ አቦምሳ፣ ሜኢሶ፣ ጨለንቆ፣ ሐሮማያ፣ ቁሉቢ፣ ደንገጎ፣ መልካጀብዱ፣ ካራሚሌ፣ ኩርፋጨሌ፣ ሀሮዶየ፣ ሰዲቃ፣ አሽ፣ ኩሚ፣ ትንሹሜጢ፣ ተርጫ፣ ሀዋሳ፣ ይርጋለም፣ ወልቂጤ፣ ወንዶገነት፣ ቦረቃ እና ዲመካ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በገለምሶ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, there was cloud cover and accumulation over the northeast, east, south, southwest, and central parts of our country. In this regard, in Cheffa, Combolcha, Sirinka, Mehalmeda, Haik, Guguftu, Debresina, Kemise, Harbu, Wegdi, Ginager, Mollale, Hara, Robit, Kachise, Gore, Adama, Abomsa, Meiso, Chelenko, Haromaya, Kulubi, Dengego, Melekjbidu, Karamile, Kurfachele, Harodoye, Sedika, Ashi, Kumi, Tineshumetti, Tercha, Hawassa, Yirgalem, Welkite, Wondogenet, Borka, and Dimeka received light to moderate (1-29) amount of rainfall. Additionally, in Gelemso heavy rainfall exceeding 30 mm was recorded within 24 hours.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ አሪ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚኖረው የደመና ሽፋንና ክምችት ላይ በመነሳት የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ የማዣንግና አኝዋክ ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖበደሌ፣ ሆሮጉድሩና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ሰሜንና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ ባሌ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀቤና ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን ሸዋ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
Tomorrow, there will be cloud cover across the southern parts of the country which are in their second rainy season of the Bega. In association with this, from Southern Ethiopian region Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Ari, and Gedeo zones, the zones of the Sidama region, and from Oromia region Gujina and West Guji zones will receive light rain in a few places. In addition, based on cloud cover and accumulation, light to moderate rainfall (1–29 mm) is anticipated over Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo, and Dawuro zones; Majang and Aniak zones; Jimma, Ilubabor, Bunobedele, Horogudru, and East Wellega; West, north, and Southwest Shewa; Bale, Arsi, and West Arsi; West and East Hararge zones; Gurage, Silte, Kebena Special Zone; Hadiya, Halaba, Yem Special Zone; Kembata and Tembaro zones; East and West Gojjam; south Gondar; North Shewa; and North and South Wollo zones.