Daily Weather Report 25 December 21

Weather Summary for previous day

Dec. 20, 2025

በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ ምዕራብና በምስራቅ ኦሮሚያ፤ በደቡብና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፤ በጋምቤላ፣ በምስራቅ አማራ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በኮምቦልቻ፣ ስሪንቃ፣ ጨፋ፣ መሀልሜዳ፣ አለምከተማ፣ የትኖራ፣ ጋቲራ፣ ጭራ፣ አዳማ፣ አቦምሳ፣ ገለምሶ፣ አደሌ፣ ደሎመና፣ ነገሌ፣ ቡሌሆራ፣ ሞያል፣ ኩርፋጨሌ፣ ጨለንቆ፣ መልካጀብዱ፣ ሐረር፣ ድሬዳዋ፣ አሽ፣ ማሻ፣ ማጅ፣ ወላይታሶዶ፣ አርባምንጭ፣ ጂንካ እና ኮንሶ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡

Yesterday, there was cloud cover and accumulation over the southern, western, and eastern Oromia; south and southwestern Ethiopia; Gambella; eastern Amhara, and eastern parts of the country. In this regard, light to moderate rainfall (1-29 mm) was recorded in Kombolcha, Srinka, Cheffa, Mehalmeda, Alemketema, Yetnora, Gatira, Chira, Adama, Abomsa, Gelemso, Addele, Delomena, Negele, Bulehora, Moyal, Kurfachele, Chelenko, Melkajebdu, Harar, Dire Dawa, Ashi, Masha, Maji, Wolaitassodo, Arba Minch, Jinka, and Konso.

Weather Forecast for next day

Dec. 22, 2025

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜን ምስራቅና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ አሪ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ የአኝዋክ እና ማዣንግ ዞኖች፤ የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ቡኖበደሌ፣ ሆሮጉድሩና ምስራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ሰሜንና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ የጉራጌ፣ ቀቤና ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ የምስራቅና ምዕራብ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን ሸዋ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የደቡብና ደቡብ ምስራቅ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የፋንቲ፣ አውሲ እና ሀሪ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈን፣ ኤረርና ጃራር ዞኖች በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ ስለሆነም ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች ማህበረሰቡ የደረሱ ሰብሎችን መሠብሠብ እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ይጠቁማል።

Tomorrow, there will be cloud cover accumulation across the southern parts of the country which are in their second rainy season of the Bega, as well as in the southwest, central, northeast, and eastern parts of the country. In this regards, from south Ethiopian region Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, Ari, and Gedeo zones, Sidama region zones and from Oromia region Guji and west Guji zones will receive light rain in a few places. Additionally, in Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo, and Dawro zones; Agnuak and Majang zones; Jimma, Ilubabor, Bunobedele, East Wellga, west, southwest, north and east Shewa, Arsi and west Arsi, Bale, west and east Hararge zones; Harar; Dire Dawa; Gurage, Kebena special zones, Hadiya, Halaba, Yem Special zones, Kembata and Tembaro zones; east and west Gojjam, south Gondar, north Shewa, Oromo Special zones, north and south Wollo zones; southern and southeastern zones of the Tigray region; Fanti, Awsi, and Hari zones of the Afar region; and from Somali region Siti, Fafen, Erer, and Jarar zones will have light to moderate rainfall (1-29 mm) in some areas. Therefore, the Ethiopian Meteorology Institute advises communities in areas expecting unseasonal rainfall to harvest matured crops.