Daily Weather Report 25 December 19

Weather Summary for previous day

Dec. 18, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በደቡብ፣ በደቡብምዕራብ፣ በምዕራብ፣ በመካከለኛው፣ በሰሜንምስራቅና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሻምቡ፣ አርጆ፣ ጎሬ፣ ጋቲራ፣ ጭራ፣ ሊሙገነት፣ ጅማ፣ ሶኮሩ፣ አጋሮ፣ ቢላምቢሎ፣ ቡልቡል፣ ፉጎሌቃ፣ መቱ፣ ሀሮዶዮ፣ ቡሌሆራ፣ ትንሹሚጢ፣ ቅዳሜ ገበያ፣ መንደር-11፣ ማሻ፣ አማን፣ ተርጫ፣ ወላይታሶዶ፣ ሳውላ፣ አንጋጫ፣ ዲመካ፣ ይርጋለም፣ ወልቂጤ፣ ቡልቂ፣ ወንዶገነት፣ ሀዋሳ፣ ሐረር፣ ማጀቴ፣ ጨፋ፣ ኮምቦልቻ፣ መርሳ፣ ሀይቅ፣ ደብረሲና፣ ማርየ፣ አቀስታ፣ ጭፍራ፣ ኤሊዳር፣ መሆኒ እና ኮረም ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29ሚ.ሜ) መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በተጨማሪም በጂንካ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday, there was cloud cover and accumulation in the south, southwest, west, central, northeast, and eastern parts of our country. In this regard, in Shambu, Arjo, Gore, Gatira, Chira, Limugenet, Jimma, Sokoru, Agaro, Bilambilo, Bulbul, Fugoleka, Metu, Harodoye, Bulehora, Tinshumit, Kidamegebeya, Village-11, Masha, Aman, Tercha, Wolaitasodo, Sawla, Angacha, Dimeka, Yirgalem, Welkite, Bulki, Wondogenet, Hawassa, Harar, Majete, Cheffa, Combolcha, Mersa, Haik, Debresina, Mariye, Akesta, Chifra, Elidar, Mehoni and Korem received light to moderate rainfall (1-29 mm). Additionally, in Jinka heavy rainfall exceeding 30 mm was recorded within 24 hours.

Weather Forecast for next day

Dec. 20, 2025

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ በጥቂት የቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ እና ሊበን ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚኖረው ጠንካራ የደመና ሽፋንና ክምችት ላይ በመነሳት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲና ምዕራብ አርሲ፣ ባሌና ምስራቅ ባሌ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀቤና ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምስራቅ ጎጃም፣ ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን ሸዋ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ዋግኸምራ፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ ጋቢ፣ አውሲ እና ሀሪ ዞኖች፤ እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ፣ ፋፈንና ጃራር ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የሚኖራቸው ሲሆን፤ በራያ አላማጣ፣ ቆቦ፣ ጉባላፍቶ፣ ዳዋጨፋ፣ ጉሊና፣ ድሬዳዋ፣ ቀርሳ፣ ሜታ፣ ጭናክሰን፣ ሐሮማያ፣ ሐረር፣ ጉርሱም፣ ቱሎ፣ አሴኮ እና ጎሎልቻ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ30 ሚሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ። ስለሆነም ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሚኖርባቸው አካባቢዎች ማህበረሰቡ የደረሱ ሰብሎችን መሠብሠብ እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ይጠቁማል።

Tomorrow, there will be Cloud coverage and accumulation across the southern and southeastern parts of the country which are in their second rainy season of the Bega. Accordingly, light rainfall is expected in some areas of Borena, Guji and west Guji zones; from southern Ethiopian region Wolaita, Gofa, Gamo, Basketo, South Omo, and Gedeo zones; Sidama region zones and from Somali region Dawa and Liben zones. Additionally, due to intensified cloud cover and accumulation, from southwest Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, West Omo, and Dawro zones; Jimma, West, Southwest, and East Shewa, Arsi and West Arsi, Bale and East Bale, West and East Hararge zones; Harar and Dire Dawa; from Central Ethiopian region Gurage, Silte, East Gurage, Kebena Special Zone, Hadia, Halaba, Yem Special Zone, Kembata, and Tembaro zones; from Amhara region including East Gojjam, South Gondar, North Shewa, Oromo Special Zones, Waghemra, North and South Wollo zones; southern, southeastern, and eastern Tigray zones; from zones of Afar region Kilbeti, Fanti, Gabi, Awsi, and Hari zones; and Somali region including Siti, Fafen, and Jarrar zones will have light to moderate rainfall (1-29 mm), while The numerical forecasts indicate that Raya Alamata, Kobo, Gubalafto, Dawachefa Gulina, Dire Dawa, Kersa, Meta, Chelenko, Haromaya, Harar, Gursum, Tulo, Aseko, and Gololcha will receive exceeding 30 mm of heavy rainfall within 24 hours. Therefore, the Ethiopian Meteorology Institute advises communities in areas expecting unseasonal rainfall to harvest matured crops.