Daily Weather Report 25 December 18
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ደቡብ የሀገሪቱ አከባቢዎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በማይጨው፣ መሆኒ፣ ኮረም፣ ጭፍራ፣ ዳሊፋጊ፣ ወገልጤና፣ መርሳ፣ ሀይቅ፣ ደጋን፣ ጉንዶመስቀል፣ ካቺሴ፣ ፍቼ፣ ሻምቡ፣ አንገርጉትን፣ ነቀምቴ፣ ጨዋቃ፣ አርጆ፣ በደሌ፣ ጎሬ፣ ጋቲራ፣ ጋምቤላ፣ ቢላምቢሎ፣ ፉጎሌቃ፣ ኢጃጂ፣ ፍንጫዓ፣ አደሌ፣ ወልቂጤ፣ ቢላቴ፣ ቡልቂ፣ ዲመካ፣ ወንዶገነት፣ ዲላ፣ ጂንካ እና ኮንሶ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡
Yesterday, cloud coverage was observed over the northeast, central, western, southwestern, and southern parts of the country. Consequently, Maichew, Mehoni, Korem, Chifra, Dalifagi, Wegeltena, Mersa, Haik, Degan, Gundomeskel, Kachise, Fiche, Shambu, Angergutin, Nekemte, Chewaka, Arjo, Bedele, Gore, Gatira, Gambella, Bilambilo, Fugoleka, Ijaji, Fincha’a, Adelle, Welkite, Bilate, Bulki, Dimeka, Wendogenet, Dilla, Jinka, and Konso received light to moderate rain.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ አሌ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከኦሮሚያ ክልል በጥቂት የቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ አርሲ እና ባሌ ዞኖች ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል በጥቂት የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ ጋቢ፣ አውሲ እና ሀሪ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
For the upcoming day, the south and southeast parts of our country, which are in their second rainy season of the Bega, will have cloud coverage. Associated with this, from the south Ethiopian region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, south Omo, Ale, and Gedeo zones; Sidama region zones, and a few Borena, Guji, and west Guji, west Arsi, and Bale zones of Oromia region will receive light rainfall. Besides, due to the strengthening rain-bearing weather events, from the south west Ethiopian region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; a few Agnuak and Majang zones of the Gambella region; from Oromia region Jimma, west, north, south west and east Shewa, Arsi, west and east Hararge zones; Harar; Dire Dawa; from the central Ethiopian region Gurage, Silte, Kebena special zone, east Gurage, Mareko special zone, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from Amhara region east Gojjam, north Shewa, Oromo special zone, north and south Wollo zones; from Tigray region south, southeast and east zones; from Afar region Kilbeti, Fanti, Gabi, Awusi and Hari zones and from Somali region Siti and Fafen zones will experience light to moderate (1-29 mm) unseasonal rainfall at some places.