Daily Weather Report 25 December 17

Weather Summary for previous day

Dec. 16, 2025

በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ ምዕራብና መካከለኛው ኦሮሚያ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በጋምቤላ፣ በምስራቅ አማራ፣ በደቡብና ደቡብ ምስራቅ ትግራይ፣ በአፋር እና በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በቡሌሆራ፣ አምቦ፣ ካቺሴ፣ ወሊሶ፣ ሻምቡ፣ ፍቼ፣ ፍንጫዓ፣ ሐዋሳ፣ ቢላቴ፣ ወንዶገነት፣ ዲመካ፣ ጂንካ፣ ቡልቂ፣ ሳዉላ፣ ተርጫ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ኮንሶ፣ አማን፣ ቴፒ፣ ሆሳዕና፣ እምድብር፣ ወራቤ፣ ጋምቤላ፣ ፉኝዶ፣ ትንሹሜጢ፣ ጉበቲ፣ ቅዳሜገበያ፣ ሲቦ፣ አሺ፣ ሙጊ፣ ኩሚ፣ ወገልጤና፣ ጋሸና፣ ጊሽራቤል፣ መንዲዳ፣ ኮምቦልቻ፣ ደ/ሲና፣ ጉጉፍቱ፣ ወራኢሉ፣ እነዋሪ፣ ደብረብርሃን፣ መሆኒ፣ ኮረም፣ ጭፍራ፣ ሰመራ እና ሐረር ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለዉ ዝናብ አግኝተዋል፡፡

Yesterday, southern, western, and central Oromia, Sidama, southern, southwestern, and central Ethiopia, Gambella, eastern Amhara, southern and southeastern Tigray, Afar, and the eastern parts of the country had cloud coverage. Consequently, Bulehora, Ambo, Kachise, Weliso, Shambu, Fiche, Fincha’a, Hawassa, Bilate, Wendogenet, Dimeka, Jinka, Bulki, Sawula, Tercha, Walaita, Sodo, Konso, Aman, Tepi, Hosaina, Emdibir, Werabe, Gambella, Fugnido, Tinishu Meti, Gubeti, Kidame Gebeya, Sibo, Ashi, Mugi, Kumi, Wegeltena, Gashena, Gishrabel, Mendida, Kombolcha, D/Sina, Guguftu, Werailu, Enewari, Debrebrehan, Mehoni, Korem, Chifra, Semera and Harar received light to moderate rainfall.

Weather Forecast for next day

Dec. 18, 2025

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በደቡብ ምዕራብ፣ መካከለኛው፣ ሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ምዕራብ አርሲ እና ባሌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች እና የሲዳማ ክልል ዞኖች በአንዳንድ ስፍራዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚኖረው የደመና ሽፋን ላይ በመነሳት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል በጥቂት የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምዕራብ እና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ማረቆ ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች፤ ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ ጋቢ፣ አውሲ እና ሀሪ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሲቲ እና ፋፈን ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, better cloud coverage and accumulation are expected over the south and southeastern parts of our country, which are in their second rainy season of the Bega, as well as the southwest, central, northeast, and east parts of our country. In this respect, from Oromia region Borena and east Borena, Guji and west Guji, west Arsi and Bale zones; from the south Ethiopia region, Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, South Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji, and Gedeo zones, and the Sidama region zones will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall in some places. Furthermore, due to the cloud coverage, from the south west Ethiopia region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; a few Agnuak and Majang zones of Gambella region; from Jimma, Ilubabor, west, north, south west and east Shewa, Arsi, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from the central Ethiopia region Gurage, Silte, Kebena special zone, east Gurage, Mareko special zone, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from Amhara region east Gojjam, north Shewa, Oromo National special zone, north and south Wollo zones; from Tigray region the south, southeast and east zones; from Afar region Kilbeti, Fanti, Gabi, Awusi and Hari zones, and from Somali region Siti and Fafen zones will experience light to moderate unseasonal rainfall.