Daily Weather Report 25 December 16

Weather Summary for previous day

Dec. 15, 2025

በትናንትናው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ መካከለኛው እና ሰሜን ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በሞያሌ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ቢላቴ፣ ሐዋሳ፣ ወንዶገነት፣ አንጋጫ፣ ዉልበርግ፣ ዲመካ፣ ተርጫ፣ አማን፣ ቴፒ፣ ጋምቤላ፣ አሺ፣ ሙጊ፣ ጎሬ፣ አይራ፣ አርጆ፣ ጅማ፣ ሊሙገነት፣ ሶኮሩ፣ እምድብር፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ጋሸና፣ እነዋሪ እና ማይጨው ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡

Yesterday, cloud coverage was observed over the south and southeast parts of the country, which are in their second rainy season of the Bega, as well as the west, southwest, central, and northeast parts of the country. Along with this, Moyale, Walaita Sodo, Bilate, Hawassa, Wendogenet, Angacha, Wulberg, Dimeka, Tercha, Aman, Tepi, Gambella, Ashi, Mugi, Gore, Aira, Arjo, Jimma, Limugenet, Sokoru, Emdibir, Hosaina, Werabe, Gashena, Enewari, and Maichew received light to moderate rainfall.

Weather Forecast for next day

Dec. 17, 2025

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋንና ክምችት ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ባሌ እና ምዕራብ አርሲ ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ ዞን በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ከቀላል እስከ መካከለኛ (1-29 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት ዝናብ ሰጭ የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ፣ ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ድሬዳዋ፤ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከአማራ ክልል የምዕራብና ምስራቅ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች እና ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ ጋቢ፣ አውሲ እና ሀሪ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡

Tomorrow, the south and south-eastern parts of our country, which are in their second rainy season of the Bega, will have cloud coverage and accumulation. In connection with this, from the south Ethiopian region, the Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, south Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji, and Gedeo zones; Sidama region zones; from Oromia region Guji and west Guji, Borena and east Borena, Bale and west Arsi zones, and from Somali region Dawa zone will receive light to moderate (1-29 mm) rainfall at some places. Moreover, due to the strengthening rain-bearing weather events, from the south west Ethiopian region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from Gambella region Agnuwak and Majang zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, west, north, south west and east Shewa, Arsi, west and east Hararge zones; Addis Ababa; Harar; Dire Dawa; from central Ethiopia region Gurage, Silte, east Gurage, Kebena special zone, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from Amhara region west and east Gojjam, north Shewa, Oromo national special zone, north and south Wollo zones; from Tigray region the south, southeast and east zones and from Afar region Kilbeti, Fanti, Gabi, Awusi and Hari zones will experience light to moderate unseasonal rainfall.