Daily Weather Report 25 December 15
Weather Summary for previous day
በትናንትናው ዕለት በደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ እና ምዕራብ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የደመና ነበራቸው፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በያቤሎ፣ ቡሌሆራ፣ ነገሌ፣ ደሎመና፣ ወላይታ ሶዶ፣ ተርጫ፣ ፉኝዶ፣ መንደር-11፣ አሺ፣ ጅማ፣ ቡልቂ፣ ዲመካ እና ወልቂጤ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የተስተዋለ ሲሆን፤ በጥቂት የሀገሪቱ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ 5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ተመዝግቧል፡፡
Yesterday, cloud coverage was observed in the southern, south-western, and western parts of the country. In this regard, Yabelo, Bulehora, Negelle, Delomanna, Walaita Sodo, Tercha, Fugnido, Mender-11, Ashi, Jimma, Bulki, Dimeka, and Welkite. On the other hand, dry, sunny, and windy Bega weather was observed in the north eastern, central, and eastern areas of the country; accordingly, the minimum temperature of the day was recorded below 5 degrees Celsius in a few highlands of the country.
Weather Forecast for next day
በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ የሀገራችን አከባቢዎች ላይ የተሻለ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጂ፣ ቦረናና ምስራቅ ቦረና፣ ምዕራብ አርሲ እና ባሌ ዞኖች፤ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጎፋ፣ ጋሞ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጋርዱላ፣ ኮሬ፣ አሌ፣ ኮንሶ፣ ቡርጂ እና ጌዲኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የዳዋ ዞን በአንዳንድ ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በሌላ በኩል ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶች ላይ በመነሳት ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ፣ ስልጤ፣ ምስራቅ ጉራጌ፣ ቀበና ልዩ ዞን፣ ሀድያ፣ ሀላባ፣ የም ልዩ ዞን፣ ከምባታ እና ጠምባሮ ዞኖች፤ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የቤንች ሸኮ፣ ሸካ፣ ከፋ፣ ኮንታ፣ ምዕራብ ኦሞ እና ዳዉሮ ዞኖች፤ ከጋምቤላ ክልል የአኙዋክ እና ማጃንግ ዞኖች፤ ከኦሮሚያ ክልል የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ምዕራብ፣ ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ሸዋ፣ አርሲ እና ምዕራብ ሐረርጌ ዞኖች፤ አዲስ አበባ፤ ሐረር፤ ከአማራ ክልል የምዕራብ ጎጃም፣ ሰሜን ሸዋ፣ የኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን፣ ሰሜን እና ደቡብ ወሎ ዞኖች፤ ከትግራይ ክልል የደቡብ፣ ደቡብ ምስራቅ እና ምስራቅ ዞኖች እና ከአፋር ክልል የቅልበቲ፣ ፋንቲ፣ ጋቢ እና ሀሪ ዞኖች ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን (1-29 ሚ.ሜ) ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡
For the next day, the south and southeast parts of our country, which are in their second rainy season of the Bega, will have better cloud coverage. Associated with this, from Oromia region Guji and west Guji, Borena and east Borena, west Arsi and Bale zones; from the south Ethiopia region Walaita, Gofa, Gamo, Basketo, south Omo, Gardula, Kore, Ale, Konso, Burji and Gedeo zones; Sidama region zones and the Dawa zone of the Somali region will receive light rain in some places. Conversely, due to the strengthening weather events, from the central Ethiopia region Gurage, Silte, east Gurage, Kebena special zone, Hadiya, Halaba, Yem special zone, Kembata and Tembaro zones; from the south west Ethiopian region Bench Sheko, Sheka, Kefa, Konta, west Omo and Dawuro zones; from Gambella region Agnuak and Majang zones; from Oromia region Jimma, Ilubabor, west, south west and east Shewa, Arsi and west Hararge zones; Addis Ababa; Harar; from Amhara region west Gojjam, north Shewa, Oromo national special zone, north and south Wollo zones; from Tigray region the south, southeast and east zones and from Afar region the Kilbeti, Fanti, Gabi and Hari zones will experience light to moderate (1-29 mm) unseasonal rainfall.