Daily Weather Report 25 December 13

Weather Summary for previous day

Dec. 12, 2025

በትናንትናዉ ዕለት በደቡብ፣ በደቡብምዕራብና በምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ነበራቸዉ፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ በጂንካ፣ ቡርጂ፣ ያቤሎ፣ ሞያሌ፣ ዴሎ ሜና፣ ሙጊ፣ ኪዳሜ ገበያ እና ትንሹ ሜጢ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ አግኝተዋል፡፡ በሌላ በኩል በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ የበጋዉ ደረቅ፣ ፀሃያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ ተስተዉሎባቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም በደብረብርሀን፣ አምባ ማርያም ቡኢ እና ቁሉቢ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሽየስ በታች ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

Yesterday the southern, south‑western and western parts of our country were covered by a layer of clouds. Along with this, light rain fell in Jinka,Burji,Yabelo, Moyale, Dello Mena, Mugi, Kidame Gebeya and Tinshu Metti. Meanwhile, the northern‑eastern, central and eastern areas of the country experienced the typical Bega dry, sunny and windy weather. In addition, Debre Berhan, Amba Mariam,Bui and Kulubi recorded daytime low temperatures below 5 degrees Celsius.

Weather Forecast for next day

Dec. 14, 2025

በነገው ዕለት በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት በደቡብና ደቡብ ምስራቅ እንዲሁም በምዕራብ እና በደቡብ ምዕራብ የሀገሪቱ አከባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ፣ ጋሜ፣ ጎፋ፣ ኮሬ፣ ኮንሶ፣ ባስኬቶ፣ ደቡብ ኦሞ እና ጌድኦ ዞኖች፤ የሲዳማ ክልል ዞኖች፣ ከኦሮሚያ ክልል የጉጂና ምዕራብ ጉጅ፣ ቦረናና ምስረቅ ቦረና ዞኖች እና ከሶማሌ ክልል የሊበን፣ ዳዋ እና አፍዴር ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ ቀላል መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም ከሚጠናከሩት የአየር ሁኔታ ክስተቶቸች በመነሳት በጥቂት የጅማ፣ ኢሉባቦር፣ ሸካ፣ ቤንች ሸኮ፣ ዳውሮ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ኮንታ፣ ከፋ፣ አኝዋክ፣ ማጃንግ፣ አዊ፣ ደቡብ እና ሰሜን ወሎ ዞኖች በጥቂት ቦታዎቻቸው ላይ አነስተኛ መጠን ያለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ይኖራቸዋል፡፡ በሌላ በኩል የሰሜን፣ ሰሜን ምስራቅ፣ መካከለኛው እና ምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፣ ፀሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታ የሚስተዋል ሲሆን በአንዳንድ ደጋማ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5°C በታች እንደሚሆን የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

Tomorrow during the daytime, a second rainy period will bring cloudy conditions to parts of the country in the south and southeast, as well as the west and southwest. In connection with this, light rain is expected in a few places of these zones of Southern Nations, Nationalities, and Peoples’ Region: Wolayita, Gamo, Gofa, Kore, Konso, Basketo, South Omo, and Gedeo; in parts of Sidama region; in the Oromo region: Guji and western Guji, Borena and south-western Borena; and in parts of the Somali region: Liben, Dawa and Afder. Additionally, due to evolving weather disturbances, light, unexpected rainfall is likely in isolated locations of the following zones: Jimma, Illubabor, Sheka, Bench Sheko, Dawuro,West Omo,Konta,Kefa,Agnuak,Majang,Awi,South and North Wollo. Elsewhere over the northern, northeast, central and eastern parts of the country dry, sunny and windy conditions are expected during the day. Forecast information also indicates that in some highland areas daytime low temperatures may fall below 5°C.